የደሴ ከተማ አስተዳደር በዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ግንባታ ላይ ስልጠና ሰጠ።

የደሴ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የስማርት ሲቲ ግንባታ ለማፋጠንና ዘመናዊ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቴክኒክ ስልጠና ለአመራሮችና ለባለሙያዎች ሰጥቷል።

​በስልጠናው መክፈቻ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የደሴ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም አበራ እንደገለጹት፤ ከተማዋን ወደ ስማርት ሲቲ ለመቀየር ከተጀመሩ ዘመናዊ አሰራሮች መካከል የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ግንባታ አንዱና ዋናው ነው።

የስልጠናው ዋና ዓላማም ለአመራሩና ለቴክኒክ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የፕሮጀክቱን ትግበራ በተቀናጀ መልኩ ማጠናከር እንደሆነ አስገንዝበዋል።

​ሥራ አስኪያጁ አክለውም፣ ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየር፣ ለከተማዋ ነዋሪዎች ዘመናዊ፣ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

​የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ምንነት፣ ጠቀሜታና የአተገባበር ሂደትን አስመልክቶ በዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ፕሮጀክት ማናጀር በአቶ አግማሴ ገበየሁ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ ተሰጥቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top