በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር የተገነባው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስን ጨምሮ የክልልና የሰሜን ጎጃም ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ጥላሁን በምረቃው ላይ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢን ይፈጥራል። መሰል የልማት እንቅስቃሴዎች በዞኑ ሌሎች ከተሞችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የመርዓዊ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ብርሃኑ አበረ በበኩላቸው፤ የቡርቃ ኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበትና የጽዳት ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መሆኑን ጠቁመው፣ ለስኬቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ነዋሪዎች፣ ባለሃብቶችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስን ጨምሮ የክልልና የዞን አመራሮች የተገነባውን የኮሪደር ልማት የጎበኙ ሲሆን፣ የከተማዋን የልማት እንቅስቃሴና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመልክቷል።

